Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ኮል ቲያን ማዊን ጋር በወቅታዊ የአገሪቱ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ነቢል የሁለቱ አገራት ግንኙነት በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ መሆኑን በመግለጽ በይበልጥ ለማጎልበት አገራቱን በንግድ ማስተሳሰር ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪ አምባሳደሩ በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ኮል ቲያን በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኑነት በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
እንዲሁም ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ ዘርፍ ተመጋጋቢ አቅም ያለቸው በመሆኑ ይህን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል በቅድሚያ አገናኝ አውራ መንገድ መገንባት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች በደቡብ ሱዳን ካለው በርካታ የኢኮኖሚ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሕዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገራት የኃይል ቋት እንደሚሆንና ይህም ለኢንደስትሪ ልማት ወሳኝ ግብዓት መሆኑን አውስተዋል።
የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ችግር በውይይት ለመፍታት ጥረት ማድረግ ተገቢ መሆኑን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.