Fana: At a Speed of Life!

ለኢሰማኮ እጩ ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና ለሌሎች ኮሚሽነሮች የቀረበው የሹመት የውሳኔ ሃሳብ ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እጩ ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና ሌሎች ኮሚሽነሮች ላይ የቀረበውን የሹመት የውሳኔ ሃሳብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ፡፡
ተሿሚዎቹ ዝርዝር የስራ ልምዳቸውን በመመልከት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ሰብሳቢነት በሚመራው የእጩ አቅራቢዎች ኮሚቴ ከታየ በኋላ ነው ሹመቱ እንዲፀድቅ የቀረበው፡፡
በእጩ አቀራረብ ሂደትም ግልፅ የህዝብ ማስታወቂያ ጥሪ ተደርጎ ከህዝብ ጥቆማና በራስ አመልካችነት በአጠቃላይ 253 ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡
ኮሚቴውም በከፍተኛ ጥንቃቄ ከመረመረ በኋላ መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሟሉ አራት እጩዎችን መርጦ ነው ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ያቀረበው፡፡
ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ከተመለከተ በኋላ
1. ወይዘሮ ራኬብ መሰለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር
2. ወይዘሮ መስከረም ገስጥ የሴቶችና ህፃናት መብቶች ጉዳይ ኮሚሽነር
3. ወይዘሮ ርግበ ገብረሃዋሪያት የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ጉዳይ ኮሚሽነር
4. ዶክተር አብዲ ጂብሪል የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ጉዳይ ኮሚሽነር እንዲሆኑ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር የወጣ አዋጅ 521/1993ን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡
በሃይለኢየሱስ ስዩም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.