Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በዴልታ ዝርያ ኮቪድ 19 ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በ80 በመቶ አሻቀበ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የዴልታ ዝርያ ባለው የኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር በ1ወር ውስጥ ብቻ በ80 በመቶ ማሻቀቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

በወሩ በአፍሪካ በኮቪድ 19 ምክንያት ሕይወታቸውን ያለፈ ሰዋች ቁጥር 24 ሺህ 987 ሲሆን÷ ከባለፈው ወር ሕይወታቸውን ካጡ 13 ሺህ 242 ሰዎች አንፃር የአሁኑ በ89 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ነው የተገለፀው፡፡

ቫይረሱ ከቀደሙት ዝርያዎች አንፃር በመስፋፋት ፣ በመግደል ባህሪው ከፍተኛና አስደንጋጭ እንደሆነ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ያመላከተው፡፡

እስካሁን ድረስም ቫይረሱ በ132 ሀገራት መሰራጨቱንና የመግደል አቅሙም 80 በመቶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንደዓለም ጤና ድርጅት መረጃ  በዴልታ ዝርያ ኮቪድ 19  እስካሁን ድረስ 4ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ እና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታትም አሃዙ ከ200 ሚሊየን ሊያልፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ:- ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.