7ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ አውደ ርዕይ ከመጭው ሃሙስ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
አውደ ርዕዩ የህብረት ስራ ግብይት ለሰላም ግንባታ በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፥ የተለያዩ ማህበራት ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋና በጥራት እንደሚቀርቡበት ተገልጿል።
በህብረት ስራ ማህበራት መካከል ጠንካራ የገበያ ትስስር መፍጠርና ማህበራት ለሰላም መስፈንና ለትብብር የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ በተጨባጭ ለማሳየት ታልሞ እንደሚካሄድ የፌደራል የህብረት ሥራ ኤጄንሲ አስታውቋል።
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው አውደ ርዕይ 175 የህብረቱ ማህበራትና አጋር ድርጅቶች የሚሳተፉ ይሆናል።
ከ50 ሺህ በላይ ጎብኝዎች ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።