የዓለም ባንክ የአፍሪካ ሀገሮችን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ፕሮጀክት መንደፉን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገሮችን ኢኮኖሚ በ3ነጥብ 3 በመቶ ለማሳደግ ፕሮጀክት መንደፉን አስታወቀ፡፡
የአፍሪካ “የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከቻይና ፈጣን እድገት ጋር ሲነፃፀር በ2021 የመጀመሪያ አጋማሽ የአፍሪካን የወጪ ንግድ ሊያጠናክር ይችላል” ተብሏል፡፡
ዓለም አቀፉ አበዳሪ ድርጅት የዓለም ባንክ ብድር ፥ የኢኮኖሚ ዕድገትን በ2022 እና በ 2023 ከ 4 በመቶ በታች ተግባራዊ ያደርጋል ነዉ የተባለዉ፡፡
ከ2020 በኋላ የአፍሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ እንደተጎዳ ጥናቶች አሳይተዋል ተብሏል፡፡
“ውጤታማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት ህይወትን ለማዳን እና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ማገገም ቁልፍ ሚና እንዳለዉ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ አገራት ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ ክስተት አንስቶ የመዋቅር እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ማጎልበታቸውን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ የማገገም ሂደት ለማፋጠን የዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በሻምበል ምህረት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!