የባሕልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ የሥራ ርክክብ አደረጉ
አዲስ አበባ፣መስከረም 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲሱ የመንግስት ምሥረታ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከቀድሞዋ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
በርክክቡ ወቅትም ለሚኒስትሩ ስለ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አደረጃጀትና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች እንዲሁም ለወደፊት የታቀዱ እቅዶች በዶክተር ሂሩት ካሳው ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡
አቶ ቀጀላ መርዳሳ÷ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በመመደባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው የኢትዮጵያን ገፅታ ሊቀይር የሚችል ሥራን ለመሥራት የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ካለው አመራርና ሠራተኛ ጋር በመወያየት በትጋት ለመወጣት እንደሚተጉ ገልፀዋል፡፡
የሚኒስቴሩ አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበልም ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡