Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ህብረት መደበኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአስፈፃሚ ም/ቤት ጉባዔ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአስፈፃሚ ምክርቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው።

የህብረቱ የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን÷ በጉባዔው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርሰቶፌ ሉቱንዱላ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

አቶ ደመቀ ከመደበኛው ስብሰባ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያካሄዱ ይጠበቃል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.