Fana: At a Speed of Life!

በሚኒስቴሩ የለሙ 13 የኤሌክሮኒክ አገልግሎቶች ምረቃና ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የለሙ 13 የኤሌክሮኒክ አገልግሎቶች ምረቃና የአገልግሎቶቹን ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ባለስልጣን ለደንበኞቹ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ ለተገልጋዮቹ ባሉበት ተደራሽ ለማድረግ ያስለማቸው 13 የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ማቅረቢያ ዘዴዎች በዛሬው እለት ተመርቀው ርክክብ ተፈጽሟል።
አገልግሎቶቹ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ ዘርፍ በኩል የለሙ ናቸው።
አገሎግሎቶቹን የዘርፉ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ሲናሞ እና የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በጋራ አስጀምረዋል።
እንደ ዶክተር አብዮት የለሙት አገልግሎቶቹ ከፈቃድ አሰጣጥ አና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚኖሩ አላስፈላጊ ምልልሶችና ወጪዎችን በመቀነስ ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ የሚያስችሉ ከመሆናቸውም ባሻገር የመስርያቤቱን ውጤታማነት የሚያሻሽሉ ናቸው።
ዶክተር አብዮት አክለውም የአገልግሎቶቹ መልማት ብቻውን ግብ ስለማይሆን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የአመራርና የባለሙያዎች ክትትል ያስፈልጋል።
በዚህ ረገድ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በበኩላቸው፥ ባለስልጣኑ የንግድ ትስስሩን በቴክኖሎጂ አስደግፎ እየሰራ እንዳለ ገልጸው የለሙት አገልግሎቶች የደንበኞችን እርካታ በእጅጉ ያሳድጋሉ ብለዋል።
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአገልግሎቶቹን ቀጣይነት እና ተደራሽነት ማረጋገጥና የሚሰጡ ሙያዊ ድጋፎች እንዲቀጥሉ የሚያስችል ስምምነት በባለስልጣን መስርያቤቱና በሚኒስቴር መስሪያቤቱ መካከል መፈረሙን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People reached
63
Engagements
Boost Post
61
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.