Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ልጅ ላይ የ33 ሚሊየን ዶላር ቅጣት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ልጅ ቴዎዶሪን ኦቢያንግ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት የ33 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ተላለፈባቸው።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቅጣቱ የተላለፈባቸው የህዝብን ገንዘብ ለራሳቸው ቅንጡ ህይወት በማዋል እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በአፍሪካ ለረዥም ጊዜ በስልጣን ላይ በመቆየት የሚጠቀሱት ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ኦባሚያግ ንጉማ ልጅ የሆኑት ኦቢያንግ 33 ሚሊየን ዶላር እንዲከፍሉ የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሀብታቸው ከሕጋዊ ምንጮች የተገኘ መሆኑን በመግለጽ ክሱን ውድቅ ቢያደርጉም ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

የ50 ዓመቱ ቲኦዶሪን ኦቢያንግ ከፈረንጆቹ 2000 እስከ 2011 በፈረንሳይ 25 ሚሊየን ዮሮ የሚያወጣ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርታምን ጨምሮ ሌሎች  ቅንጡ ንብረቶች ባለቤት መሆኑ ተጠቁሟል።

እንዲሁም 18 ቅንጡ መኪናዎች ፣ የስነ ጥበብ ስራዎች ፣ ጌጣጌጦች እና ሌሎች ንብረቶች በፈረንሳይ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ተገልጿል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ምክትል ፕሬዚዳንቱ የግል ጀት ፣ የማይክል ጃክሰን ማስታወሻዎችን እና የቅንጦት እቃዎችን ለመግዛት የሀገሪቱን የነዳጅ ዘይት መዝረፉን ነው የሚገልፀው።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.