የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአፍሪካ ሲቪል አሺዬሽን ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአፍሪካ ሲቪል አሺዬሽን ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ፀሃፊ አቶ ተፈራ መኮንንበዛሬው እለት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በዚሁ ወቅት አቶ ተፈራ፥ የኢትዮጰያ ሲቪል አቪዬሽን የዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ደህነንት ደረጃን መቶ በመቶ ማሟላቱ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን የምርመራ ቡድን በቅርቡ መረጋገጡን በማስታዋስ በአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ስም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላፈዋል።
በመንግስት በኩል ለተሰጠው አመራርም አድናቆታቸውን የገለፁት አቶ ተፈራ፥ ይህንን ስምና ዝና በዘለቄታው ጠብቆ ለማዝለቅ በመንግስት በኩል የሚደረገውን ክትትል እና ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል።
አቶ ተፈረ በተጨማሪም፥ አንድ አፍሪካዊ የአየር ትራንስፖርት ግብይት ለመመስረት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ እና በሌሎች ክልላዊ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የአቪዬሽን እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ለአቶ ገዱ ገለጻ እና ማብራሪያ አድርገዋል።