Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሸሸና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ በጋራ እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ከሀገር የሸሸና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ እንዲሁም በተያያዥ ወንጀሎች ላይ በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሸሸ እና የተመዘበረ ሃብትን ለማስመለስ…

በ300 ሚሊየን ብር ለሚገነባ የመድሃኒት ማከማቻ መጋዘን የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ በ300 ሚሊየን ብር ወጪ የመድኃኒት ግብዓት ማከማቻ መጋዘን እና የአስተዳደር ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ የመሰረት ድንጋዩን  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ እና የጤና ሚኒስትር  ዶ/ር መቅደስ ዳባ…

ከዳያስፖራው 3 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር መላኩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዳያስፖራው የሚገኘውን ሬሚታንስ ለማሳደግ በተደረገ ድጋፍና ክትትል 3 ቢሊየን ዶላር የሬሚታንስ ገቢ መገኘቱን የዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በዳያስፖራ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ላይ ከኢፌዴሪ ሚሲዮኖች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡…

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ሲምፖዚዬም በዘርፉ ያላትን ተሞክሮ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዶሚኒካን ሪፐብሊክ በተዘጋጀው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ሉላዊ የአፈፃፀም ድጋፍ ሲምፖዚዬም ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ አካፍላለች፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን…

በኮሎምቢያ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜናዊ ኮሎምቢያ ገጠራማ ስፍራ ላይ በተከሰተ የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡ የኮሎምቢያ ጦር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ሄሎኮፕተሯ በሰሜናዊ ኮሎምቢያ የሽምቅ ተዋጊዎችን እና የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎችን…

በአማራ ክልል የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር ሰላም አስፈላጊ ነው – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር ሰላም አስፈላጊ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ…

ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንሌይ አቻ ሲለያይ ሼፍልድ ዩናይትድ መውረዱን አረጋገጠ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኒውካስልና ዎልቭስ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ተለያየ፡፡ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስል ሼፍልድ ዩናይትድን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ዎልቭስ…

በፕሪሚየርሊጉ ሊቨርፑል ወሳኝ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የዋንጫ ተፎካካሪ የነበረው ሊቨርፑል ከዌስትሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡ በምሳ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ጃሮድ ቦውን እና ሚሸል አንቶኒዮ የዌስተሃም ጎሎችን ሲያስቆጥሩ አንዲ ሮበርትሰን እና አልፌንሴ አሪዮላ(በራሱ ላይ)…

በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመሆን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ በውድድሩ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር መቅደስ ዓለምሸት 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡ አያል ዳኛቸው…

አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደግፍ  የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደግፍ  የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡ “ኢትዮጵያ-ታምርት፤ እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ሃሰብ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪዎች…