Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመሆን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ በውድድሩ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር መቅደስ ዓለምሸት 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡ አያል ዳኛቸው ከባድ ፉክክር አድርጋ በ16 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ፥ ለተሰንበት ግደይ ሦሰተኛ ደረጃ እንዲሁም ውብርስት አስቻለ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡ በተጨማሪም በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ሰለሞን ባረጋ 12 ደቂቃ ከ55…
Read More...

አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲዳስ ኩባንያ ባዘጋጀው አዲዜሮ የ5ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡ የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር ያሸነፈችው፡፡ በዚሁ ውድድር አትሌት መልክናት ውዱ ሁለተኛ እንዲሁም…

ሌስተር ሲቲ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2022/23 የውድድር ዘመን ሳይጠበቅ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የወረደው ሌስተር ሲቲ በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል። ቀበሮዎቹ ትናንት ምሽት ሊድስ ዩናይትድ በኪው ፒ አር 4 ለ 0 መረታቱን ተከትሎ ነው ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሯቸው በወረዱበት ዓመት ወደ ሊጉ መመለስ የቻሉት። በቀጣይ ኢፕስዊች ታዎን…

በማንዴላ መታሰቢያ ውድድር ውጤት ላስመዘገበው ቡድን አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ የማንዴላ መታስቢያ ውድድር ላይ በመሳተፍ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ቦክስ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ ሲመለስ አቀባበል ተደረገለት። ቡድኑ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ቢልልኝ…

ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል ኤምባሲው ደስታውን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደስታውን ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በደርባን በተካሄደው የቦክስ ውድድር ላይ ሦስት የብር እና ሦስት የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ሁሉንም ተወዳዳሪዎችና የልዑካን ቡድን አመራሮች…

 በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ ሁለቱንም የባህርዳር ከተማ ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር÷ የወልቂጤን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፉዓድ አብደላ አስቆጥሯል፡፡ በውጤቱ መሰረትም የጣና ሞገዶቹ…

በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ሜዳሊያ በመሰብሰብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሶስት ብርና ሶስት የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳልያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሱራፌል አላዩ፣ ሚሊዮን ጨፎ እና ቤተል ወልዱ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ቤተልሄም ገዛህኝ፣ ሮማን አሰፋ እና ተመስገን ምትኩ ደግሞ…