Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ካሜሩን ለሚያደርገው ጉዞ በስካይ ላይት ሆቴል የተሰናዳው የሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። ዋልያዎቹ በሀገር ባህል ልብስ አሸብርቀው በስፍራው የተገኙ ሲሆን፥ የመንግሥት ባለስልጣናት ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ መታደማቸዉን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል። አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ …
Read More...

ሀዋሳ ላይ ሲደረግ የነበረው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዘጠኝ የጨዋታ ሳምንታትን ያስተናገደው የሃዋሳ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ይሆናል። ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ባህር ዳር ከነማ ከአዳማ ከነማ ጋር 9፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የቀድሞው የባህር ዳር ከነማ አሰልጣኝ ፋሲል…

በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 25 ተጫዋቾች ዝርዝር ታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉት 25 ተጫዋቾችን ይፋ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ አህጉራዊ ውድድር መመለሱ ይታወቃል። ዋልያዎቹ በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ካሜሩን፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡርኪና ፋሶ ጋር መደልደላቸው…

በፕሪሚየር ሊጉ ሃዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2 ለ 0 አሸንፎታል። ምሽት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና በሃዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የጎዳናና የአገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በታይዋን በተደረገ የታይፒ ማራቶን ውድድር በወንዶች ደመቀ ካሰው 2 ሰአት ከ11 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ መሰረት…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል። ዛሬ በተካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ወላይታ ዲቻን ባገናኘው የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በተደረገ…

በስፔን እና በሜክሲኮ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በስፔን በተደረገ የማላጋ ማራቶን ውድድር በሴቶች÷ አትሌት ፅግነሽ መኮንን አንደኛ፣ ያይንአበባ እጅጉ ሁለተኛ እንዲሁም ማሪቱ ከተማ አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሜክሲኮ…