Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማንን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ ባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማንን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቱን አስታውቋል። ክለቡ ወጣቱን አሰልጣኝ ለውጥ ፍለጋ በሚል እንዳሰናበታቸው ደይሊ ሜይል አስነብቧል። የቀድሞው የቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ፒ ኤስ ጂ እና ቼልሲ አሰልጣኝ የነበሩት ቶማስ ቱሼል የባቫሪያኑን ክለብ ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኔግልስማን ሙኒክን በፈረንጆቹ 2021 በአሰልጣኝነት ተረክበው ቡንደስሊጋ እና የጀርመን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን ከክለቡ ጋር አሸንፈዋል። ሙኒክ በቡንደስሊጋው…
Read More...

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሔራዊ ቡድን 197 ጊዜ በመሰለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል፡፡ የ38 ዓመቱ አጥቂ ትናንት ምሽት ሀገሩ ፖርቹጋል ሌችተንስታይንን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ በመሰልፍ ሁለት ጎሎችን በቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ በጨዋታው መሰለፉን ተከትሎ ሮናልዶ ለሀገሩ 197 ጨዋታዎችን…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ዛሬ ምሽት ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ በካዛብላንካ መሐመድ 5ኛ ስታዲየም የሚደረገው ጨዋታ ምሽት 5፡30 የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ መርሐ ግብሩን ለማከናወን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን…

ሜሱት ኦዚል ጫማ መስቀሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል በ34 አመቱ ከእግር ኳስ ዓለም ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡ በጀርመኖቹ ሻልከ 04 እና ዌርደር ብሬመን የተጫወተው ኦዚል በ2010 የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ከጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጋር ባሳየው ድንቅ ብቃት የስፔኑን ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ መቀላቀል ችሏል፡፡…

የኢትዮጵያ አጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺህ ሜትር መሰናክል፣ እርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ለአትሌቶች የውድድር እድል መፍጠር እንዲሁም የክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማት አትሌቶች…

ዋልያዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1ለ0 አሸንፏል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ 10 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አካሂዷል፡፡ በጨዋታውም ዋልያዎቹ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡ ግቡን…

ስፖርት ማህበራዊ ግንኙነት የሚጠናከርበት መድረክ ነው- አምባሳደር  መስፍን ቸርነት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ስፖርት ማህበራዊ ግንኙነት የሚጠናከርበት የዲፕሎማሲ መድረክ ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተናገሩ፡፡ 8ኛው የመላ አማራ ስፖርት ውድድር  በጎንደር ከተማ በይፋ ተጀምሯል። በዚህ ወቅት የባህልና ስፓርት ሚኒስትር  ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት እንዳሉት÷ ስፖርት በትውልድና…