የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ስነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል እየተካሄደ ነው፡፡
የብፁዕነታቸው አስከሬን በቅድስት ስላሴ ካቴደራል የፀሎተ ፍትሃት፣ ስርዓተ ማህሌትና ጸሎተ ኪዳን ሲደረግለት አድሮ በአሁን ሰዓት ወደ አውደ ምህረት ወጥቶ በሊቃውንት ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ወረብ እየተደረገለት ይገኛል።
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉ ባኤ አገኘው ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የአማራ ክልል ርዐሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የተለያዩ የዓለም ሀገራት አብያተ ክርስቲያናት እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢምባሲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኃይማኖት ኢያሱ