ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግል ህትመት እና ቁሳቁስ ግዥ መጠናቀቁን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ የህትመት እና የቁሳቁሶች ግዥ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ቦርዱ ቁሳቁሶቹን ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ መጋዘን አስገብቶ ማጠናቀቁን በመግለፅ የቁሳቁስ ድልድል ስራ በቅርቡ እንደሚጀምር ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የተከለሰ አጠቃላይ የምርጫ ሰሌዳ መሰረት የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሆኗል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ የድምፅ መስጫ ቀን ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑ የሚታወስ ነው።
የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም የሚቀርቡ ጥያቄዎች ግንዛቤ ውስጥ ቢገቡም ከህግ አንፃር የድምፅ መስጫ የተከለሰው ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision