Fana: At a Speed of Life!

አሽራፍ ጋኒ በድጋሚ የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሽራፍ ጋኒ በድጋሚ የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

አሽራፍ ጋኒ ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ በአፍጋኒስታን የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ 50 ነጥብ 64 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነው በድጋሚ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት።

በዚህ መሰረትም ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አፍጋኒስታንን የሚያስተዳድሩ ይሆናል።

የቅርብ ተቀናቃኛቸው አብደላህ አብደላህ ደግሞ 39 ነጥብ 53 በመቶ ድምጽ ማግታቸው ተገልጿል።

ባሳለፍነው ዓመት የተካሄደው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ተቃዋሚዎች በምርጫ ሂደቱ ላይ ቅሬታ በማቅረባቸው ምክንያት ለአምስት ወራት ሳይገለጽ መቆየቱ ይታወቃል።

ምንጭ፦https://www.foxnews.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.