Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ ለ20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን እና በትንንሽ ቀዳዳዎች ብቻ የሚሰጠውን የውስጥ አካል ህክምና ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓመታት ተቋርጦ የቆየው ሆድ ሳይከፈት በትንንሽ ቀዳዳዎች የሚሰጠው የቀዶ ጥገና ህክምና (ላፓሮስኮፒ) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደገና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ለ20 አመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ሆድ ሳይከፈት በትንንሽ ቀዳዳዎች ብቻ የሚሰጠው የውስጥ አካል ህክምና (ላፓሮስኮፒ) ከእስራኤል በመጣው የህክምና ቡድን ድጋፍ እንደገና መጀመሩን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።

ይህ የህክምና አገልግሎት ከእስራኤል በመጣው የህክምና ቡድን መጀመሩ ተመላክቶ ከዚህ በኋላም ሙያውን በተማሩ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች እየተሰጠ እንደሚቀጥል መገለፁን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.