ከተመድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ሰርዋ ቴቴ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ሰርዋ ቴቴ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡
በውይይታቸው ወቅት በቀጠናው ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በተወሰደው የተኩስ አቁም ውሳኔ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
በቀጠናው ባሉ ድንበር ዘለል የፀጥታ ፈተናዎች እና መሰል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡