አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተገለፀ።
አቶ አቤ ሳኖ በዛሬው እለት በአምባሳደርነት የተሾሙትን የቀድሞውን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊናን ተክተው ስራቸውን መጀመራቸው ተነግሯል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን በማገልገል ላይ እንደበሩ ይታወቃል።
ፕሬዚዳንቱ አቶ አቤ ሳኖ ለፋና ብሮድካሰቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከዚህ ቀደም ከጥር 1998 እስከ ታህሳስ 2001 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግለው እንደነበረ አስታውሰዋል።
በአሁኑ ወቅት መንግስት የሰጣቸው ሹመት ወደ ቀድሞ ቤታቸው እንደመመለስ መሆኑንም ተናግረዋል።
አዲሱ ተሿሚ ለባንኩንም ሆነ ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት በትኩረት ለመስራት እንደሚጥሩ ገልጸዋል።
በታሪክ አዱኛ