ለውጡን ተከትሎ በወጡ ሕጎች ላይ በሚታዩ የተፈጻሚነት ክፍተቶች ላይ ጥናት አድርጎ ምክረ-ሀሳብ የሚያቀርብ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ለውጡን ተከትለው ከወጡ ሕጎች መካከል በዘጠኙ ላይ በሚስተዋሉ የተፈጻሚነት ክፍተቶች ላይ ጥናት በማድረግ ምክረ-ሀሳብ የሚያቀርብ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የክልል ፍትህ ቢሮዎች ባዘጋጇቸው የጠበቆች፣ የሲቪክ ማህበራ ድርጅቶች፣ የአስተዳደር ሥነ-ስርዓት አዋጅ እና የማረሚያ ቤቶች የአስተዳደር ረቂቅ ህግን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ፣ የአስተዳደር ስነ-ሥርዓት አዋጅ፣ የጠበቆች አዋጅ፣ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዋጅ፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች አዋጅ፣ የሚዲያ አዋጅ፣ በሰዎች የመነገድ እና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል አዋጅ፣ የንግድ ህግ እና የጸረ-ሽብር አዋጅ ጥናት የሚደረግባቸው ሕጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለምአንተ አግደው÷ ለውጡን ተከትሎ ከወጡ የህግ ማዕቀፎች ውስጥ በተለዩ 9 ሕጎች ላይ ተፈጻሚነታቸውን የሚገመግመው ዓብይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመንግስት ሕግ እና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ የሚመራው ይህ ኮሚቴ÷ ህጎቹ ከወጡ በኋላ ለወጡበት ዓላማ መዋላቸውን በጥልቀት የሚመረምር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በጥናቱ ያገኛቸውን መነሻ ችግሮች እና ችግሮቹ ሊፈቱ እና የህጎቹን ተፈጻሚነት የሚያረጋግጡ ምክረ ሃሳቦችን ይዘው ይቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገ ነው የገለጹት፡፡
ኮሚቴው ስራውን በስኬት እንዲያጠናቅቅ ፍትህ ሚኒስቴር ተገቢውን ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ አንደሆነ መግለጸቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡