Fana: At a Speed of Life!

የኮይሻ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት አፈፃፀም 61 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የኮይሻ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት አፈፃፀም 61 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።
የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አባይነህ ጌታነህ እንዳሉት፥ በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ በዓመት 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሮጀክቱ እያንዳንዳቸው 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ 6 ተርባይኖች የሚገጠሙለት ሲሆን፥ የተርባይኖች ቤት ፣ የማስተንፈሻ ስራው ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ተጠቅሷል።
የፕሮጀክቱ የሲቪል ስራ 52 በመቶ፣ የግድቡ አርማታ ሙሌት 30 በመቶ፣ ማስተንፈሻው 13 በመቶ የደረሰ ሲሆን ኤሌክትሮሜካኒካል ስራው በጥናት ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
አጠቃላይ አፈፃፀሙ 61 በመቶ መጠናቀቁን ኢንጂነር አባይነህ አስረድተዋል።
ፕሮጀክቱ ለአምስት ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርም ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከተ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.