Fana: At a Speed of Life!

ዓየር መንገዱ ወደ ማልታ የቻርተር በረራ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ማልታ የመጀመሪያውን የቻርተር በረራ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

በቻርተር በረራው ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ጎብኚዎች መካተታቸውን የዓየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ፣ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ክፍል ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ እንዲሁም ሌሎች እንግዶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.