Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና በፈፀሟቸው የዲሲፕሊን ጥሰቶች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ በ3ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በክለብ ደረጃ ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ3ኛ ሳምንት ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ክለቡ 5 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡና ከባህርዳር ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኞች እና የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋችን አጸያፊ ስደብ መስደባቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህ መሰረትም የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ እግርኳሽ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ክለቡ 50 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም ኮሚቴው ለሻሸመኔ ከተማ የቡድን መሪ እና ዋና አሰልጣኙ አቶ ፀጋዬ ወንድሙ ከዲሲፕሊን ጥስት ጋር በተያያዘ ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.