Fana: At a Speed of Life!

ሲዳማ ቡና ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሻሸመኔ ከተማን የገጠመው ሲዳማ ቡና 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የሲዳማ ቡናን የድል ጎሎች ደስታ ዮሐንስ ፣ ደግፌ አለሙ እና አበባየሁ ዮሐንስ ሲያስቆጥሩ÷ የሻሸመኔ ከተማን ብቸኛ ጎል እዬብ ገ/ማርያም አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተክትሎ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያሳካ አዲስ አዳጊው ሻሸመኔ ከተማ በአራት ጨዋታዎች ተሸንፎ የሊጉ ግርጌ ላይ ተቀምጧል፡፡
የፕሪሚየርሊጉ 4ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 12 ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.