Fana: At a Speed of Life!

ፊፋ 32 ክለቦች የሚሳተፉበት የዓለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) 32 ቡድኖች የሚሳተፉበት የዓለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በቻምፒዮንስ ሊጉ በተለያዩ ዙሮች ተሳትፎ ያደረጉ ክለቦችን የሚያካትተው ይህ ውድድር በፈረንጆቹ 2025 ከሰኔ 15 እስከ ሀምሌ 13 በአሜሪካ እንደሚደረግ ነው የተገለፀው፡፡

የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የውድድር ፕሮግራሙ መደበኛ የሊግ እና ዓለም አቀፋዊ ጨዋታዎችን በማይነካ መልኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

በውድድሩ 32 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን ከተለያዩ አህጉራት ከሚገኙ ስድስት ኮንፌዴሬሽኖች የተውጣጡ ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተመላክቷል፡፡

12 የአውሮፓ ክለቦች በውድድሩ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

በአራት ዓመታት ውስጥ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱት ቼልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ያለምንም ማጣሪያ በውድድሩ የሚሳተፉ ክለቦች መሆናቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በቻምፒዮንስ ሊጉ በተከታታይ ዓመታት ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩት ባየር ሙኒክ፣ ፓሪስ ሴንት ዠርመን፣ ኢንተር ሚላን፣ ፖርቶ እና ቤኔፊካ በውድድሩ በቀጥታ የሚሳተፉ ክለቦች መሆናቸውን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.