Fana: At a Speed of Life!

የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆኗል።

በጥሎ ማለፉ የጣሊያኑ ሮማ ከሆላንዱ ፊይኖርድ እንዲሁም ሌላኛው የጣሊያን ክለብ ኤሲሚላን ከፈረንሳዩ ሬንስ ጋር ተገናኝተዋል።

የፈረንሳዩ ሌንስ ከጀርመኑ ፍሬይቡርግ የስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ከስፖርቲንግ ሊዝበን እንዲሁም ቤኔፊካ ከቱሉዝ ይጫወታሉ።

ብራጋ ከቃራባግ፣ ጋላታሳራይ ከስፓርታ ፕራግ እንዲሁም ሻካታር ዶኔስክ ከማርሴይ በጥሎ ማለፉ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.