Fana: At a Speed of Life!

ኧርሊንግ ሃላንድ የቢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ የቢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርት ፐርሰናሊቲ ሽልማትን አሸንፏል፡፡

ኖርዌያዊው አጥቂ ክለቡ ማንቼስተር ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫ ባሳካበት የ2022-23 የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊግ፣ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኤፍ ኤ ካፕ ውድድሮች 52 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ወጣቱ አጥቂ በ38 ጨዋታዎች 36 ጎሎችን በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን የወርቅ ጫማ ሽልማት ማሸነፉም አይዘነጋም፡፡

ሃላንድ ከሽልማቱ በኋላ ባስተላለፈው መልዕክት “ያለፈው የውድድር ዘመን አስደናቂ ነበር፣የሶስትዮሽ ዋንጫን ከቡድን አጋሮቼ ጋር አሳክቻለሁ፣የቢቢሲ ስፖርት ሰዎች ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ” ብሏል፡፡

በዘርፉ የደቡብ አፍሪካዋ የራግቢ ቡድን አምበል እና የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ሲያ ኮሊሲ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ የሶስት ጊዜ የፎርሙላ 1 የዓለም ሻምፒዮን ማክስ ቬርስታፔን ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

የአራት ጊዜ የኦሊምፒክ ጅምናስቲክስ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ሳይመን ቢልስ፣ የስፔን ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ኦይታና ቦንማቲ እና የ24 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊው ኖቫክ ጆኮቪች በዘርፉ በእጩነት መቅረባቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስታወሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.