Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጹ፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት የበለጠ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ያለው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ÷ ፎረሙ አዳዲስ ባለሀብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው አስገንዝበዋል፡፡

በፎረሙ በኢትዮጵያ ያሉ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን በተመለከተ ለሩሲያ ባለሃብቶች ዝርዝር ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የፖሊሲ ማሻሻዎች፣ ለባለሀብቶች ስለሚደረጉ ማበረታቻዎች እንዲሁም ኮምሽኑ ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢን ለመፍጠር እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራት ገለፃ አድርገዋል፡፡

የሩሲያ የተለያዩ አምራች ኩባንያዎች ተወካዮች በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

በፎረሙ የኩባንያዎቹ ተወካዮቹ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸውን የፕሮጀክት ዕቅዶችም ለተሳታፊዎች ማቅረባቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.