Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ እግርኳስ ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን መዛወር እንደማይፈልግ ባለስልጣናቱ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን እንዲዛወሩ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የሞስኮ እግርኳስ ባለስልጣናት ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በፊፋ እና ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች አንዳይሳተፉ ማዕቀብ ተጥሎባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ማዕቀቡን ተከትሎ በማንኛውም የሀገራት ውድድር እየተሳተፈ የማይገኘው የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች በኤሲያ ኮንፌዴሬሽን ውድድሮች ለመሳተፍ የሩሲያ እግርኳስ ባለስልጣናት ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሩሲያ አግርኳስ ህብረት በዛሬው እለት እንዳስታወቀው÷47 አባላት ባሉት የኤሲያ ኮንፌዴሬሽን ለመሳተፍ ቀደም ሲል በሩሲያ እግርኳስ ባለስልጣናት የቀረበው ሃሳብ ውድቅ ተደርጓል ብሏል፡፡

“ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን ለመዛወር የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ተቃውመናል፤ሩሲያ አውሮፓ ናት፤በፊፋ እና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች ለመሳተፍ አሁንም እንታገላለን” ብሏል ህብረቱ በመግለጫው፡፡

የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች በፊፋ እና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊጎች እንዲሳተፉ ከፊፋ ጋር ንግግር መጀመሩን ያስታወቀው የሩሲያ እግርኳስ ህብረት በንግግሩ አንፃራዊ ለውጦች መኖራቸውን ገልጿል፡፡

የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን በተጣለበት ማዕቀብ ምክንያት በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እንዳይሳተፍ የተደረገ ሲሆን ÷የሩሲያ የእግርኳስ  ህብረት ከፊፋ ጋር የሚያደርገው ድርድር የሚሳካ ከሆነ ሩሲያ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ልትሳተፍ እንደምትችል አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.