Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ  እና አስቶንቪላ አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡

9፡30 ከሜዳው ውጭ ሉተን ታውንን የገጠመው ቼልሲ 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

ኑኖ ማዱዌኬ እና ኮል ፓልመር (ሁለት) የቼልሲን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ኤሊያህ አደባዮ እና ሮዝ ባርክሌይ የሉተንን ሁለት ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

እንዲሁም 12፡00 ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ በሮድሪ እና ጁሊያን አልቫሬዝ ሁለት ጎሎች ሼፊልድ ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሲቲዝኖቹ አርሰናልን በጎል ክፍያ በመብለጥ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ሌላኛው የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን አስቶንቪላ ከበርንሌይ ከባድ ጫና ቢገጥመውም 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ብሬንትፎርድን 3 ለ 1፣ ዎልቭስ ኤቨርተንን 4 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.