Fana: At a Speed of Life!

በማህበር ተደራጅተው የ70/30 የቤት ግንባታ ለመጀመር ቦታ የወሰዱ ነዋሪዎች ሥራ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማህበር ተደራጅተው የ70/30 የቤት ግንባታ ለመጀመር ቦታ የወሰዱ ነዋሪዎች ግንባታ እንዲጀምሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ 20/80 እና 40/60 ተመዝግበው እጣ ሲጠባበቁ የነበሩ ነዋሪዎችን በማህበር አደራጅቶ የ70/30 ዕድል ማመቻቸቱ ይታወሳል፡፡

57 ማህበራት ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተመስርተው 4 ሺህ 500 ነዋሪዎች ተደራጅተው የቦታ ርክክብ የተደረገ ቢሆንም እስካሁን ወደ ስራ መግባት አለመቻላቸውን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የፍርድ ቤት እግድ፣ የካሳና የመብራት ምሰሶዎች አለመነሳት ግንባታው እንዲጓተት አድርገውታልም ነው የተባለው፡፡

ሆኖም ግን የካሳ፣ የፍርድ ቤት እግድና ክስ የሌለባቸው ወደ አስር የሚጠጉ ማህበራት በመኖራቸው ግንባታውን መጀመር እንዳለባቸው ቢሮው ጠቁሟል፡፡

የቢሮው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ማህበራቱም ግንባታውን ለመጀመር በራሳቸው የሚያደርጉት ጥረት ሊኖር ይገባልም ነው የተባለው፡፡

በመሆኑም በየካቲት ወር ምንም እክል የሌለባቸው ማህበራት ወደ ቤት ግንባታ መግባት እንዳለባቸው ቢሮው አሳስቧል፡፡

የማህበራቱ ተወካዮችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የቤት ግንባታው እንዳይጓተት እገዛ ሊያደርጉልን ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በዘቢብ ተክላይ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.