Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ያፀድቃል፡፡

የም/ቤቱን 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ እና 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤዎች መርምሮ በማፅደቅ የዕለቱን መደበኛ ስብሰባ የሚጀምር ይሆናል፡፡

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት ከ1ኛ ልዩ ስብሰባ የተሸጋገሩ የተለያዩ አጀንዳዎችንም መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

ከተሸጋገሩት አጀንዳዎች ውስጥ የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የፕላን፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ደንቡን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት እንዲሁም የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የሚቀርብ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.