Fana: At a Speed of Life!

አየር ሃይል ዘመኑ የደረሰበትን ትጥቅ እስከመታጠቅ የደረሰ የሀገር ኩራት ተቋም ሆኗል – ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አየር ሃይል ዘመኑ የደረሰበትን ትጥቅ እስከመታጠቅ የደረሰ የሀገር ኩራት ተቋም ነው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ70ኛ ቃኘው ኮርስ ዕጩ መኮንኖችና አሰልጣኞች በአየር ሃይሉ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ÷ አየር ሃይሉ የረጅም ዘመን ታሪክ ያለው አንጋፋ ተቋም መሆኑን አውስተዋል፡፡

ለውጡን ተከትሎ በተቋሙ ላይ በተሰራው የሪፎርም ትግበራ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ተላቆ ቀድሞ ወደነበረበት ከፍታው ለመመለስ የተሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተሰራው ጠንካራ ሥራ አየር ሃይሉ የሀገራችንን ሉዓላዊነት ወደሚያረጋግጥበት ቁመናው ተመልሷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባሻገርም አየር ሃይሉ ዘመኑ የደረሰበትን የአየር ሃይል ትጥቅ እስከመታጠቅ የደረሰ የሀገር ኩራት የሆነ ተቋም ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አሁን የደረሰበት የእድገት ደረጃ እንዳስደነቃቸው አንስተዋል፡፡

የተቋሙ እድገትና የወደፊት ራዕይ ከፍተኛ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው መናገራቸውንም ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.