Fana: At a Speed of Life!

ከ275 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ275 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ከየካቲት 1 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 188 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገቢና 87 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች የያዘው፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ድሬድዋ፣ አዳማ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ ተገልጿል፡፡

ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 6 ተጠርጣሪዎች እና 3 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia #customcomission

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.