Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴር መ/ቤቶች በ2ኛው የመካከለኛ ዘመን የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በሁለተኛው የመካከለኛ ዘመን የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ውይይቱን ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የሌሎች ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ናቸው፡፡

የተቋማቱ ተወካዮች የጋራ በሆኑ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፣ ዋና ተግባራት፣ ፕሮግራሞች እና ቅንጅት ላይ እንዲሁም የተቋማቱ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለፃ ቀርቦ ውይይት አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በመድረኩ ላይ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ትግበራ የትኩረት አቅጣጫዎች እና የአፈፃፀም ስልቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው ÷ የተቋማቸውን ተግባራት፣ ዓበይት ክንውኖችና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን ተናግረዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ÷ የውይይት መድረኩ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ያለመ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.