Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በትምህርት ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሥርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እየተገበራቸው ያሉ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

አቶ ተመስገን በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ለተማሪዎች እና ለመማር ማስተማሩ ምቹ ተደርጎ የተደራጀውን አፍሪካ አንድነት ቁ.2 ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም÷ የትምህርት ሥርዓቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የከተማ አሥተዳደሩ እየተገበራቸው ያሉ ሥራዎች ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆኑ እና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.