Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ማሰልጠኛን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑክ የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ማሰልጠኛን ጎበኘ፡፡

ማሰልጠኛው በመስክና በክፍል ውስጥ እየሰጠ ያለውን የስልጠና ሂደት አስመልክቶ ለልዑኩ ገለፃ ተደርጓል።

ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች የሜካናይዝድ ሙያተኞች በጥራት እየሰለጠኑ መሆኑም ተገልጿል።

የቴክኖሎጂ ውጤቶቹም በመስክ ልምምድ ይወጣ የነበረውን የብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች፣ ነዳጅ፣ መለዋወጫ፣ የተተኳሽና ሌሎች ወጪዎችን ቀንሰዋል ተብሏል፡፡

ሙያተኞች የሚመረቁበት ዘመናዊ የሜካናይዝድ የሰልፍ ትርዒት ማሳያ ወረዳ የደረሰበት የግንባታ ሂደትን ጨምሮ ሰልጣኞች በተለያየ የመሬት ገፅ ላይ በቋሚና በተንቀሳቃሽ ኢላማዎች ላይ ልምምድ የሚያደርጉበት የመስክ ስልጠና ወረዳዎች በልዑኩ ተጎብኝተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ማሰልጠኛው ለሚያከናውነው የመማር ማስተማር ሂደት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.