Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ተግባራትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር ተግባራትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ይመር ከበደ ተገኝተዋል።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት በ4 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈውንና ለ150 ነዋሪዎች የሥራ ዕድል የፈጠረው የቂርቆስ ፓርክን ተመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ግንባታው ሲጠናቀቅ በአማካይ የ130 አቅመ ደካሞችን የቤት ችግር እንደሚቀርፍ የሚጠበቀውን ከመሬት በላይ ባለአራት ወለል የሆነ የመኖሪያ ሕንጻ፣ በቀን እስከ 90 ሺህ ዳቦ ማምረት የሚችለውን የበረከት ዳቦና ኬክ ማምረቻ ፋብሪካ እና የጎተራ የወጣቶች ሰብዕና መገንቢያ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.