Fana: At a Speed of Life!

ለአማራ ክልል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት የትብብርና የድጋፍ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአማራ ክልል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት የትብብርና የድጋፍ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በክልሉ የገንዘብ ቢሮ የተዘጋጀው የትብብርና ድጋፍ መድረክ “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ለዘላቂ ልማትና የሕዝብ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፣ የክልሉ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሐሪ እና የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮች በመድረኩ ተገኝተዋል።

በክልሉ የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በጀት መድቦ ከመስራት ባሻገር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ሙሉነሽ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በክልሉ በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለማገዝ በሚደረገው ጥረት የሲቪል ማህበራት አጋርነት እየተሻሻለ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዛሬው መድረክም የመንግሥትና የአጋር አካላትን ድጋፍና ትብብር በማጠናከር አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.