Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሠራን ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሠራን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ረትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ የሚያስገነባቸውን 5 ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረናል ብለዋል።

እንዲሁም ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማኅበር መንግሥት ከስድስት ዓመታት በፊት በነጻ ባስረከበው 3 ነጥብ 8 ሄክታር ላይ ያስገነባቸውን 5 ሺህ ቤቶች መርቀናል ነው ያሉት።

የሕዝባችን ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል አንዱ አማራጭ የግል አልሚዎችን ማበረታታትና በአጋርነት የምንሠራበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍም በሁሉም አማራጮች እየሠራን እንገኛለን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.