Fana: At a Speed of Life!

የተረጋጋ የፖለቲካ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር ተችሏል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመደመመጥ፣ በመከባበርና በመመካከር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከወከላቸው ሕዝብ ጋር ያደረጉትን የውይይት ግብረ-መልስ ለክልሉ ካቢኔ አካላት አቅርበዋል።

ርዕሠ መሥተዳድሩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመደመመጥ፣ በመከባበርና በመመካከር በመፍታት የተረጋጋ የፖለቲካ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በመንገድና ድልድይ ግንባታ፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ትምህርትና ጤና እንዲሁም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ለአብነትም ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት አንፃር የተጀመሩ 10 ግንባታዎች መኖራቸውን ጠቁመው÷ የተወሰኑትን በያዝነው የበጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከፀጥታ አንጻር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን አንስተው÷ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል የማሰመራት ሥራው እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም በክልሉ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በጤና ተቋማት ግንባታ፣ በሠላምና ጸጥታ፣ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ፣ በትምህርት ተቋማት ግንባታና መጽሐፍ አቅርቦት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታቸው መሆናቸውን በመጥቀስ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.