Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብየዳ ፌደሬሽን መደበኛ ጉባዔን እንድታዘጋጅ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ የብየዳ ፌደሬሽን መደበኛ ጉባዔ እንድታዘጋጅ መመረጧን የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡

2ኛው የአፍሪካ የብየዳ ፌደሬሽን መደበኛ ጉባዔ በናይጀሪያ የተካሄደ ሲሆን÷ በዚሁ መድረክ ላይ ቀጣዩን ጉባዔ ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ መመረጧን ነው ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያስታወቁት፡፡

በናይጀሪያው መድረክም ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው 90 ዓለም አቀፍ የብየዳ ባለሞያዎች መካከል በሰመር ካምፕ ፕሮግራም ተሳታፊ የሆነችው ወለላ ሰዒድ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.