Fana: At a Speed of Life!

በመውጫ ፈተና የሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመውጫ ፈተና ኩረጃና ሌሎች የፈተና ሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በፈተናው ሞባይል ስልክ ይዞ በመግባት፣ መኮረጅና የተለያዩ የፈተና ሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ ተፈታኞች ውጤት ነው የተሰረዘው፡፡

የፈተና ሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ እንደሚገለጹም ተጠቁሟል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው 2ኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119 ሺህ 145 ተፈታኞች መፈተናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

መውጫ ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ሪፎርሞች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ፈተናው ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተገቢውን እውቀትና ክህሎት መቅሰማቸውንና ብቁ መሆናቸውን ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን እንደሚመራም ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.