Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ኦስማን ዲኦን÷ ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ እየተገበራቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ገላጻ አድርገዋል፡፡

ባንኩ ባለፉት ሶስት ዓመታት 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ኢንቨስትመንት ለጤናው ዘርፍ እንዳደረገ አብራርተዋል፡፡

ኢንቨስትመንቱ በዋናነት የጤና አገልግሎቶች በወረዳ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ለጤና ማሻሻያዎች ትግበራ መዋሉ ተጠቅሷል፡፡

ዓለም ባንክ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ክትባት ማምረት እንዲጀመር ድጋፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት፡፡

ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ለማዘመን ዲጂታላይዜሽን ላይ ኢንቨስት በማድረጉና ለወደሙ ተቋማት መልሶ ማቋቋም የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረጉ ዶ/ር መቅደስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዓለም ባንክ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተገበረ የሚገኘው የጤና ተቋማት እድሳት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በመድረኩ ጤና ሚኒስቴር እና አለም ባንክ ወደፊት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸው መስኮች ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.