Fana: At a Speed of Life!

በሀሰተኛ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ56 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ቆርቆሮና ብረቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግምታቸው ከ56 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ ቆርቆሮና ቶንዲኖ ብረቶች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀናት ባደረገው የቁጥጥር ሥራ ነው 40 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቆርቆሮ እና ግምታዊ ዋጋው 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሆነ ቶንዲኖ ብረት የያዘው፡፡

እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታት ሁሉም ባላድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.