Fana: At a Speed of Life!

2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016/17 ዓ.ም የምርት ዘመን 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ከክረምት በፊት ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በብሔራዊ የአፈር ማዳበሪያ ቴክኒካል ኮሚቴ ሥር የጂቡቲ የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ንዑስ ኮሚቴም ጂቡቲ ወደብ ያለውን የሥራ ሂደት እየተከታተለ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ከፈረንጆቹ ሕዳር 3 ቀን 2023 ጀምሮ እስከ አሁን ከ939 ሺህ 560 በላይ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ጂቡቲ መድረሱም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ውስጥ 905 ሺህ 525 ነጥብ 37 ሜትሪክ ቶኑ ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዙ እና ቀሪውን የማጓጓዝ ሥራም ተጠናክሮ መቀጠሉን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ በማጓጓዝ ሥራው ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በመቅረፍ ሥራው እንዲሳለጥ እየሠራ መሆኑንም ነው ንዑስ ኮሚቴው ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.