Fana: At a Speed of Life!

በግራንድ አፍሪካን ራን ለሚሳተፉ አትሌቶች የመኪና ሽልማት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ዋሽንገተን ዲሲ በሚካሄደው የግራንድ አፍሪካ ራን ለሚሳተፉ አትሌቶች የመኪና ሽልማት መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡

ግራንድ አፍሪካን ራን በየአመቱ ጥቅምት በገባ በሁለተኛዉ ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የሚደረግ የ5 ኪሎሜትር የሩጫ ዉድድር ነዉ።

በዚህ ውድድር ለሚሳተፉ በአሜሪካ ግዙፉ የቶዮታ መኪና አከፋፋይ የሆነው አሌክሳንደሪያ ቶዮታ በዉድድሩ ላይ ለሚሳተፉ ሰዎች የመኪና ሽልማት ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

የዉድድሩ ተሳታፊዎች አንደኛም ሆነ መጨረሻ ቢወጡ የመኪና ሽልማቱን የማሸነፍ እኩል እድል ያላቸዉ ሲሆን በዉድድሩ ቀን በሚወጣ የሎተሪ እጣ የመኪናዉ አሸናፊዉ ይለያል ተብሏል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት ዉድድሩ ለቀጣዩ ወር ከግንቦት ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል።

በዚህ ውድድር ከዚህ ቀደም ደራርቱ ቱሉ፤ ቀነኒሳ በቀለ፣ጥሩነነሽ ዲባባ፣ገንዘቤ ዲባባ፣ስለሺ ስህን፣ሚሊዮን ወልዴ፣በላይነህ ዴንሳሞ፣ፋጡማ ሮባ፣ብርሃኔ አደሬ፣ቁጥሬ ዱለቻ እና ሌሎች ስመ ጥር አትሌቶች ተሳተፈውበታል፡፡

በኢዮኤል ዘሪሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.