Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የጸጥታ ተቋማት የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ የአክሲዮን ድርሻ በዛሬው ዕለት ገዝተዋል፡፡

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በዚህ ወቅት÷የመከላከያ ሠራዊቱ የተለያዩ ባለሃብቶችና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይም የፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዲሁም  የመከላከያ ሠራዊቱና የክብር አባላት የአክሲዮኑ አባል እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡

የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 459/2012 አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 3 መሰረት ለመከላከያ ሠራዊት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ማቋቋም እንደሚችል የተቀመጠውን ሕጋዊነትና የዓለም ሀገራትን ተሞክሮ መነሻ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.