Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት የተላከላቸውን መልዕክት ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ካጉታ ሙሴቬኒ የተላከላቸውን መልዕክት ተቀበሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሠዓት በኋላ ከኡጋንዳ ሪፐብሊክ የፍትሕ እና የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኖርበርት ማኦ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

በዚሁ ወቅትም ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ካጉታ ሙሴቬኒ የተላከላቸውን መልዕክት መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.